Tuesday, June 7, 2011

ለምን ይዋሻል ?


                     
አሁን ያለሁት ስታር ባክስ /starbucks/  ተብሎ በሚታወቀው በአንዱ ቡና መጠጫ ውስጥ ነው :: ጥግ ይዠ ተቀምጫለሁ :: ከአንድ ወዳጄ ጋር ለመገናኘት ስለተቃጠርን ነው ከዚህ ቦታ የተገኘሁት :፡ነጻ የኢንተርኔት አገልግሎት ስለሚሰጡ  የቀጠሮየ ሰዓት እስኪደርስ  ላፕ ቶፕ ኮምፑዩተሬን ከፍቸ መልዕክቶች እያየሁ ነው  :: ቤቱ በበርካታ ተስተናጋጅ ተሞልቷል :: ጥቂቶቹ አሜሪካውያን ሲሆኑ ባብዛኛው ግን ሐበሻ በመባል የምንታወቅ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ነን :፡
ሐበሻ : አረቦች ያወጡልን የተሳሳተ ስማችን ሲሆን  ውጥንቅጥ ድብልቅልቅ እንደማለት ነው:: ትርጉሙን የወሰዱት ኢትዮጵያ የኩሽ ልጅዎች ሳባና አቢስ ሰፍረውባት ነበርና በስማቸው ስላስጠሯት  በሳባ የሳባ ምድር በአቢስ አቢሲንያ ስትባል ኑራለች ከዚህ የተነሣ አቢሲንያ የሚለውን ” ሓበሽ” በማለት ተርጉመው እንደሰጡን የታሪክ ጸሐፊዎች ያስረዳሉ ::
በአገራችን ማኪያቶ የሚባለው አይነት “ላቴ”/ Latte /የሚሉትን እየጠጣሁ ወዳጄን እየጠበቅኩት ነው ሥራም ሳልፈታ መልዕክት እያየሁ እየላኩ ነው ::  አንድ  ከጎኔ የተቀመጠ ሰው ኤክስኩዝሚ /excuse me/አለኝ ሥራየን አቁሜ ወደ እርሱ ዞርኩ ዱ ዩ ስፒክ አምሓሪክ  ? /do you speak Amharic ?/ እንደምችል ምላሽ ሰጠሁ :፡ በጥሩ አማርኛና ጨዋነት በተላበሰ አነጋገር ጊዜ ይኖርሃል ማውራት እንችላለን ? አለኝ:: ቀጠሮ እንዳለኝ ነገር ግን ወዳጄ እስኪመጣ ማውራት እንደምንችል ነገርኩት :፡
ታያለህ አለኝ ወደ ተስተናጋጁ እየቃኘ ምኑን አልኩት አብዛኞቻችን እኮ ሐበሾች ነን ለምንድን ነው ? ቡና የምንወድ እኛ ብቻ ነን እንዴ ? አለኝ : ምናልባት ከቡናው መፈጠሪያ ስለመጣን ይሆናል አልኩት :: የቡና መፈጠሪያ ኢትዮጵያ ናት ያለው ማን ነው ? አለ ግንባሩን ኮስኮስ አድርጎ :: ይህማ የታወቀ ነው አልኩት የማውቀውን ለማስረዳት እየተዘጋጀሁ ::  
ለምን ይዋሻል ? ኢትዮጵያ ቡና ዋንኛ የገቢ ምንጯ እንደሆነ አውቃለሁ እንዲያውም በልጅነቴ “የገቢው ምንጫችን ቡና ቡና “ የሚለውን ዘፈን በአባቴ ሰባራ ሬዲዮ ባትሪዉን በፀሐይ እያሞቅን ስናዳምጥና አብረን ስንዘፍን ትዝ ይለኛል፤ ከዚህ ያለፈ የቡና መፈጠሪያው ኢትዮጵያ እንደሆነች አላውቅም ለማመንም እቸገራለሁ ምክንያቱም ፈረንጆች አንድ አዲስ ነገር ሲያገኙ ስም የሚያወጡት ግኝቱን ባገኘው ሰው ወይንም በተገኘበት ቦታ ስም ነው የሚሆነው እናም ዛሬ ፈረንጆቹ ኮፊ /coffee/ ከማለት ቡና ባሉት ነበር እንዲያውም ቡና ማለት ቃሉ ከምን እንዳመጣነው አላውቅም አለኝ ::
ቡና ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘው ኢትዮጵያ ውስጥ ከፋ በተባለው ቦታ እንደሆነ ኮፊ /coffee/ ከፋ ከሚለው መምጣቱን ስገልጥለት እጀን ጨብጦ የጠፋውን እቃ እንዳገኘ ሰው አመሰግናለሁ አመሰግናለሁ በማለት ምስጋና እንዳቀረበልኝ የእጅ ስልኬ አቃጨለ የቀጠረኝ ወዳጀ ነበር ፤  ሥራ በዝቶቦት ሊዘገይ እንደሚችል ከቀጠሮአችን ሃያ ደቂቃ ተጨማሪ እንድጠብቀው ከይቅርታ ጋር ገለጸልኝ ::
ከአዲሱ ወዳጀ ጋር ወዳቋረጥነው  ጭውውት ተመልሸ ማብራሪያየን ልቀጥል ስል ሌላ ጥያቄ ጠየቀኝ :: ኮምፑዩተር /computer/ ተጠቃሚ ነህ  ? አዎ :: ፌስ ቡክ አባል ነህ ? አዎ :: ለምን ይዋሻል ? አለኝ፤ ምኑ ? የኔ ምላሽ ነበር  እኔ የገጠመኝን ላጫውትህ :: የፌስ ቡክ ተጠቃሚ ነኝ :፡ ከብዙ ሰዎች ጋር አገናኝቶኛል በርካታ ትምህርቶችን አግኝቻለሁ ከሁሉም በላይ የድሮ የሃይስኩል ጓደኞቼን አገናኝቶኛል ::
ቤተሰቦቼ ያሉት ኢትዮጵያ ነው ከከተማ በጣም የራቀ ገጠር ውስጥ:: ትምህርቴን ለመማር የተሰቃየሁትን ሳስበው  ብዙ ጥያቄዎች በአእምሮየ ይመላለስብኛል  :: ህይወቴ በሙሉ የስቃይ ጉዞ ነው ብል ማጋነን አይደለም :: ትምህርቴን ለመማር በቀን ደርሶ መልስ የስድስትና የሰባት ሰዓት መንገድ መጓዝ ይኖርብኝ ነበር  :: የርሃቡንና ጥሙ ጉዳይ  አይነገር :: ለኔ ትልቁ ተስፋ ትምህርቴ በመሆኑ ሁሉንም ተቋቁሜ እማር ነበር :፡ ከትምህርት ቤት ትዝታየ አንዷንና ህይወቴ የተቀየረበትን ልንገርህ :
የከተማ ልጅ ነህ የገጠር ? አለኝ :: ከተማ ነው ተወልጀ የደግኩ መለስኩለት :፡ ይሁን ግዴለም ::  ቀኑ ሐሙስ ነበር  በማለት ጀመረ ሐሙስ የቀን ቅዱስ ለኔ ግን ...... አልጨረሰውም ረቡዕ  ትምህርት ውየ  ለከብቶች የሚሆን ሳር አጪጄ  ቀጣዩ ቀን ፈተና ስለነበረኝ  በጨረቃ ሳጠና አድሬ  ሊነጋጋ ሲል እንቅልፍ ጣለኝ  ከእንቅልፌ ስነቃ  አንድ ሰዓት ሁኗል :: እንዴት ልግለጽልህ ? ሰማይ ምድሩ ዞረብኝ ፈተናው የሚጀመረው ሁለት ሰዓት ላይ ነው ምምህሩ እንዳናረፍድ በጣም አስጠንቅቀውናል :: ምን ላድርግ ክንፍ አውጥቸ አልበር::  አባቴን ፈረስ እንዲፈቅድልኝ ለመንኩት እርሱ ደግሞ ነፍሱን ይማረውና ስለትምህርት ስለማያውቅ ሥራ እንደመፍታት ይቆጥረው ስለነበር ሁልጊዚ የሚመክረኝ ጠንካራ ገበሬ እንድሆን ብቻ ነው ::
ፈረሱን ለዛሬ ብቻ ፍቀድልኝ ጋልቤ ካልሄድኩ ለፈተና አልደርስም ብየ ተማጸንኩት አባቴ ግን ፍጹም ሊረዳኝ አልቻለም በመጨረሻ ሳላስፈቅድ ወስጀ ፈተናውን ተፈትኘ ቢጣላኝ እንኳን በሽማግሌ እታረቃለሁ በሚል  ፈረሱን ሰርቄ እየጋለብኩ ወደ ከተማ ሸመጠጥኩ :: እንዳዛን ዕለት በፈረስ ሩጨ አላውቅም  አንድ ሁለት ጊዜ ልወድቅ እግዚአብሔር አውጥቶኛል :: እንደምንም ለሦስት ሩብ ጉዳይ ከተማ ደረስኩ :: ፈረሱን አንድ የማውቃቸው ሰዎች ለምኘ ከነርሱ ግቢ ካሰርኩት በኋላ እየሮጥኩ ወደ ት/ቤት ስደርስ ፈተናው ተጀምሯል :: መምህሩን እንዲያስገቡኝ ጠየቅኩ ፈተናው ከተጀመረ ቆይቷል ስለዚህ መግባት አትችልም አሉኝ :: እንባ እየተናነቀኝ እባክዎን ተጨማሪ ሰዓት አይስጡኝ እንደሚያዩኝ የገጠር ልጅ ነኝ ሳጠና መሽቶብኝ አሁንም የመጣሁት በፈረስ ነው  በማለት የሆነውን ሁሉ በማስተዛዘን ነገርኳቸው በትክክል ያዳመጡኝ አይመስለኝም  ወንድሜ ዛሬ መግባት አትችልም ብለው በሩን ላዬ ላይ ዘጉብኝ :: ያለቀስኩትን ለቅሦ አልረሳውም የኪዳነ ምኅረት ቤተ ክርስቲያን  በአቅራቢያው ስለነበር ወደዚያ በመሔድ እንባ ሳይሆን ደም አለቀስኩ ::



እንባየን ጠራርጌ እንደተነሣሁ  አዕምሮየ በደንብ ማሳብ ተስኖት ነበር እንደምንም ራሴን ለማረጋጋት ሞክሬ ቤቴን ለመመለስ ወሰንኩ::  እኩለ ቀን ሊሆን ምንም አልቀረው ፈረሱን ወዳሰርኩበት ቤት አመራሁ :: ስደርስ ግን ዓለም በኔ ላይ እንዳመጸችብኝ ነው የተሰማኝ ያሰርኩት ፈረስ ከቦታው የለም ::  እንደ አበደ ሰው ሆንኩኝ ደግሞም አብጃለሁ :: ግራውን ቀኙን ብቃኝ ፈረሱ የለም :: ሰዎቹን ጠየቅኳቸው አላየንም አሉኝ ::
ምን ላድርግ የቅርብም ሆነ የሩቅ ዘመድ ከተማ ውስጥ የለኝም ለማን ላወያየው ስቅስቅ ብየ አለቀስኩ ለመንግሥት ተናግሬ አንድ ነገር ቢረዱኝ በሚል ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሳመራ የማውቃቸው ከአገር ቤት የመጡ ሁለት ወጣቶች አገኘሁ ሲያዩኝ ልደበቅ አስቤ ነበር ይሁንና ፊት ለፊት ስለተገጣጠምን አልቻልኩም በፍጥነት ወደኔ ተጠግተው ምነው ? ምን ሆንክ ?አሁን እኮ አባትክን አግኝተናቸው ሰላም እንኳን ሳይሉን ፈረሳቸውን እየጋለቡ ወደ ቤታቸው ሄዱ ምን ሁናችኋል ? አሉኝ :: ፊቴ በደስታ ፈካ  አባቴ ፈረሱን የምሸጥበት መስሎት ተከታትሎ መውሰዱ ነው ::
ልጅወቹ ምንግሥት  ወታደርነት አሰልጥኖ ለመቅጠር ባወጣው ማስታወቂያ መሰረት ሊመዘገቡ እንደመጡ አጫወቱኝ እድሉ ጥሩ እንደሆነና እኔም ልጠቀምበት እንደሚገባ መከሩኝ ፤የማስብበት አዕምሮ ስላልነበረኝ በምወደውና ተስፋየ ባልኩት ትምህርቴ ጨክኘ እኔም ከነርሱ ጋር ተመዘገብኩ ::
ወደ ወታደር ማሰልጠኛው ስንጓዝ በፈቃዴ ወደ ሞት የምሄድ ያህል ይሰማኝ ነበር ወታደራዊ ሥልጠናው ከከተማ ለመጡ ልጅዎች ትንሽ የከበዳቸው ቢሆንም በግብርና  ስንኖርን ለቆየን ድካሙ ምንም አላስቸገረንም :: ሥልጠናው እንደተጠናቀቀ በትምህርት ደረጃችን መሰረት የተለያዩ ቦታወች ተመደብን :: እኔም የአስራ አንደኛ ክፍል ተማሪ ስለነበርኩ ትምህርቴን እየተማርኩ የምሰራበት እድል አግኘሁ ::
በጪውውታችን መሃል አንድ ሰው ተከሻየን ነካ አደረገኝ የቀጠረኝ ወዳጀ ነበር :: ከአዲሱ ወዳጀ ጋር የጀመርኩት ጭውውት ስላልተቋጨ እኔም በተራየ ጥቂት ደቂቃዎች እንዲሰጠኝ በመጠየቅ ጭውውታችን ቀጠልን : ይቅርታ አለ ዐይኑ ላይ ያለው እንባ በጉንጮቹ መንታ ሁኖ እየወረደ :: ይቅርታ አሰለቸውህ : ከዚህ አገር ቁጭ ብሎ ብሦትህን የሚያዳምጥህ የለም በድጋሜ አመሰግንሃለው አለኝ ::
ምንም አታስብ ብዙ ነገር እየተማርኩ ነው የጀመርከውን ቀጥልልኝ አልኩት :፡ ጊዜህን ላለመሻማት ወታደር ቤት ሁኘ ማትሪክ ተፈተንኩ ውጤቴ ጥሩ ነበር ዩንቨርስቲ መግባት እችል ነበር ይሁንና ዲቪ ደርሦኝ ወደዚህ መጣሁ :: የኔ ነገር የተነሳሁበትን ጉዳይ ትቸ ባለፈ ነገር አደከምኩህ :: ገጠር በማደጌ ዓይናፋር ነኝ ወታደር ቤት ጥቂት ጊዜ ብኖርም ምንም ያህል አልለወጠኝም :፡በተለይም ከሴቶች ጋር አፌን ሞልቸ ማውራት እፈራለሁ የወንድ ጓደኛም ቢሆን የለኝም ሚስት ለማግባት ካሰብኩ ሰነበትኩ ግን እንዴት ተብሎ ?  የሚንቁኝ ይመስለኛል ::

         

 አንድ የተሻለ አማራጭ አገኘሁ ዘመኑ ባመጣው ፌስ ቡክ የተዋወቅኳት አንዲት አዲስ አበባ የምትኖር ኢትዮጵያዊት ከብዙ የኃሳብ ልውውጥ በኋላ ስልኳን ሰጠቸኝ  አንድ እሑድ ስፈራ ስቸር ደወልኩላት ስልኩን ያነሳው ወንድ ሲሆን ስሟን ጠቅሸ እንዲያገናኘኝ ለመንኩት በጨዋ አነጋገር አንዴ ይጠብቁ ካለኝ በኋላ ድምጿን ሰማሁት :: ማንነቴን ገልጨላት ላናግራት ስሞክር በሹክሹክታ ሌላ ጊዜ እንድደውል አሁን ከቤተሰቦቿ ጋር እንደሆነች ነገረችኝ ::
ከተወሰኑ ሰዓታት በኋላ ይቅርታ ያዘለ መልዕክት በፌስ ቡክ ላከችልኝ : ስልኩን ያነሣው ታላቅ ወንድሟ እንደሆነና   ማንነው ? ብሎ እንዳፋጠጣትም አከለችበት :: የሚመቻትን ሰዓት ጠቆመችኝ ፤እኔም ምንም ማለት እንዳልሆነ ባለችው ሰዓት እንደምደውልላት ገልጨ መልስ ሰጠሁ :: በተባለው ሰዓት ስደውል ህፃን ልጅ ነበር ያነሳው :: አባባ ! አለኝ ማሙሽ ደህና ነህ  ? እኔ ማሙሽ አይደለሁም: አቢቲ ነኝ ማነው የሚል የሴት ድምጽ ሰማሁ ስልኩን ከልጁ ተቀብላ ሃሎ አለችኝ ማንነቴን አሳውቄ ደስ የሚል ህጻን ነው አልኳት የታላቅ ወንድሟ ልጅ እንደሆነና አንተም ለከርሞ ይኖርሃል ብላ ቀልድ ቢጤ ጣል አደረገች አመሰገንኳት ::
እንግዲህ ትውውቃችን በዚህ ጸንቶ ቤተሰቦቿ ጋር ስለምትኖር በፈለግኩበት ሰዓት በስልክ ላገኛት ባልችልም በተባረከው ፌስ ቡክ እየተገናኘን የለጠፈቻቸውን ፎቶ ግራፎቿን በየጊዜው እያየሁ እጅግ በጣም ወደድኳት ከፎቶወቿ ሦስት የሚሆኑትን መርጨ በማሳጠብ ክፍሌ ውስጥ ሰቅያለሁ :: ለፍቅሬ መግለጫ የሚሆኑ አንዳንድ ነገሮችን ገዝቸ ላኩላት : ምስጋናዋ አንጀት ያርሳል ::
በመጨረሻ ቀለበት ማሰር እንዳለብንና  በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ ለመሄድ እየተዘጋጀሁ እንደሆነ ፊት ለፊት ላያት እንደጓጓሁ ገለጽኩላት :: ትንሽ መቆየት እንዳለብኝ ቤተሰቦቿ  አስቸጋሪ እንደሆኑ እስክታሳምናቸው እንድታገሳት አጥብቃ ለመነችኝ :: ኃሳቧን ተቀብየ ትንሽ ከቆየሁ በኋላ መታገስ ስላልቻልኩ ያለችኝ ሳንቲም ቋጥሬ በአብዛኛው ለእጮኛየ የሚሆኑ ስጦታዎችን ይዠ ሳልነግራት ወደ ሀገሬ በረርኩ ::
                አዲስ አበባ ሆቴል ይዠ ረፍት ካደረግኩ በኋላ በሆቴሉ ስልክ ወደ እጮኛየ ደወልኩ :: ራሷ ነበር ያነሳችው :: ማን ልበል ? አለችኝ : ማንነቴን በመግለጽ ሳላሳውቃት በመምጣቴ ይቅርታ ከጠየቅኳት በኋላ ያለሁበትን ሆቴል ነግሬያት እንዴት እንደምንገናኝ ጠየቅኳት ፤አንደበቷ ይርበተበታል::  መ ም ጣ ት የ ለ ብ ህ ም !   አሁን መገናኘት አንችልም አለችኝ አይዞሽ ቤተሰቦችሽን ሌላ ጊዜ እንነግራቸዋለን ቢያብስ ዓይንሽን ልየው ብየ ነው አልኳት :: በፍጹም አንገናኝም ብላኝ ስልኩን ዘጋች መልሸ ስደውል የደወሉላቸው ደምበኛ ከአገልግሎት መስጫ ክልል ውጪ ናቸው ይላል በተደጋጋሚ ሞከርኩ ተመሳሳይ ምላሽ ነው የማገኘው ::
   ምናልባት ድንገት ስለመጣሁ ደንግጣ ይሆናል በሚል በሚቀጥለው ቀን ደወልኩላት ስልኩ ተመሳሳይ መልስ ነው የሚሰጠው ግራ ገባኝ: ሦስተኛ ቀን አሁንም ያው ነው :፡ የምጠቀመው ትልቁን ኮምፑዩተር ነው /desk top/ ብላኝ ስለነበር ለስጦታ በገዛሁላት ላፕ ቶፕ /lap top / ኮምፑዩተር የሚቆራረጠውን የሆቴሉን ኔት ዎርክ በመጠቀም ኢሜል አደረግኩላት :: መልስ የለም ::
ከአንድ ሳምንት በኋላ ፌስ ቡክ ላይ የእርሷ ጓደኛ ከሆኑት ውስጥ አዲስ አበባ የምትኖር የአንዷን ፕሮፋይል ስመለከት ስልክ አገኘሁ :: በቀጥታ ስደውልላት ቢያንስ ቁርጤን አውቄ እንድመለስ ነው ::  ከአሜሪካ እንደመጣሁና ለብርቱ ጉዳይ እንደምፈልጋት ነገርኳት የምቀልድ ስለመሰላት ትንሽ ካንገራገረች በኋላ ፈቃደኛ ሆነች ተቃጠርን ተገናኘን ::
ዘመድ መሆኔን አስረድቸ በማግባባት ልጅቷን ታውቃት እንደሆነ ጠየቅኳት ጓደኛ መሆናቸውን ነገረችኝ ::ስልኳ እንዳስቸገረኝና ልታገናኘኝ እንድትችል ለመንኳት ችግር የለውም እንዲያውም ትላንት ባለቤቷን አግኝቸው ደህንነታቸውን ነግሮኛል አለችኝ :: አግብታለች እንዴ ? አልኳት ለመረጋጋት እየሞከርኩ ፤ እንዴ አሁንማ ቆየች እኮ አግብታ ሁለት ልጅዎች ወልዳለች ብላ ቁርጤን ነገረችኝ :: እኔም ለአንድ ሳምንት ከቆየሁ በኋላ ተመለስኩ :፡ግን ለምን ይዋሻል ? ይህን ያህል በሰው ልጅ ላይ መጫወት ተገቢ ነው ብሎ አንገቱን ደፋ ::
የዋህነቱ ያሳለፈው የፈተና ህይወት ተደማምሮ ስሜቱን እንደጎዳው ያስታውቅበታል ከዚያን ቀን ጀምሮ ጥሩ ወዳጅዎች ሆነናል ቤተ ክርስቲያን ጋብዠው አገልግሎቱን ካየ በኋላ ፍጹም የተለየ ህይወት ጀምሯል ይህን ታሪኩን እንድጽፈው ጠይቄው ከፈቀደልኝ በኋላ ለፌስ ቡክ ጓዋደኞቾ ትምህርት ይሆናል በሚል አውጥቸዋለሁ ::
 ወንድ ሁነው ሳለ በሴት ጾታ ሴት ሁነው በወንድ ጾታ የሚተዋወቁ  እኔ በአሜሪካ የዚህ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር ነኝ አውሮፓ ውስጥ እንዲህ እሰራለሁ በአፍሪካ እንዲህ እያደረግኩ ነው በተለያዩ ቦታወች ተዘዋውሬ አስተምራለሁ እንዲህ ላድርግላችሁ ከተቻለም ለዚህ ማስፈጸሚያ ይህን ያህል ገንዘብ ላኩ በማለት የዋሃንን የሚያታልሉና ውድ ጊዜን በማባከን በሰዎች የሚቀልዱ ወገኖች ተገቢ አይደለም  ያልሆናችሁትን ሁነናል የሌላችሁን አለን በማለት በራሳችሁም በሰውም አትቀልዱ ማለት እፈልጋለሁ ::
ትዳር እጅግ የተከበረ ህይዎት ነው :: በዚህ ህይወት ውስጥ እያሉ ወደሌላ መመኘትም ኃጢያት ነው :: ከእግዚአብሔርም ከትዳር አጋራችሁም ጋር ያለያያል ሰላምንም ያሳጣል ::  ለትዳር አጋራችሁም ሆነ ለራሳችሁ ታማኝ ሁኑ ::
ፌስ ቡክ መረጃ ለመለዋወጥ ለመማማር ለመመካከር ለመወያየት ለመረዳዳት ይሁን እንጅ ለእኩይ ተግባር አናውለው ::  በፌስ ቡክ ያለንን እናካፍልበት የጎደለንን እንሙላበት እንጅ ለምን ይዋሻል ?

         

16 comments:

  1. Kesis Kalehiwot Yasemalin!!

    ReplyDelete
  2. ቀሲስ ፋሲል ጥሩ ታዝበዋል ::
    በጣም ደስ የሚል ነው:: ቅርታ ይደረግልኝና ሰውየው በእውነት ኢትዮጵያ ድረስ ተንገላቱ? ያሳዝናል የርሳቸውን ደግነትና የዋህነት አቢውዝ ላደረገችው እግዚአብሄር ይቅር ይበላት አይምሮ ይስጣት እያልኩ ለባለ ታሪኩ ደግሞ እግዚአብሄር አምላክ እንደ እርግብ የዋህ ብቻ ሳይሆን እንደ እባብም ብልጥ መሆን እንዳለብን አስተምሮናልና በማስተዋል ቀሪ ጊዜወትን ቢኖሩ መልካም ይመስለኛል::
    የዘመናችንን ነጻ የsocial networking website ውስጥ ገብቶ መዋሸት በእውነቱ ከሆነ አንድም ውሸታሞች ውሸታቸው የሚታወቅ ስለማይመስላቸው ያም ደግሞ ከእውቀት ማነስ የሚከሰት ሲሆን ሌላው ተፈጥሮየ ነው የሚሉት አባባል አላቸው በተፈጥሮ ውሸታሞች ሊሆኑ ስለሚችሉ ካልዋሹ መኖር የሚችሉ አይመስላቸውም ::
    በነገራችን ላይ ብዙ የፌስ ቡክ ውሸታሞች በራሳቸው ላይ ከሚቀልዱና ራሳቸውን በራሳቸው በጥፊ ከሚያጮሉ ይመደባሉ ለምሳሌ ለስራ ሲወዳደሩ ቀጣሪው የትምህርት መረጃቸውንና የሰራ ልምዳቸውን ያዩና ከፌስ ቡኩ ማንነታቸው ጋር በማስተያየት ለኢንተርቪው ሳይደርሱ ተንሳፈው የቀሩ ጥቂቶች አይደሉም:: እንግዲህ ምን እንላለን ጨው ለራስህ ብለህ ጣፍጥ ...

    ReplyDelete
  3. ትርንጎ ከሎንደንJune 10, 2011 at 11:02 AM

    ወይ ጉድ !!የማይሰማ ነገር የለም :: ለምን ይዋሻል ? ለገንዘብ ፣ለጉራ ፣ለፈን እና በልማድ :; የስንቶች ህይወት በውሸት ተበላሸ ፤ስንቶችስ ህይወታቸውን አጡ ? ይህ ልጅ በብስጪት ርምጃ ቢወስ ኑሮ የስንት ሰው ህይወት ይመሰቃቀል ነበር :: የዚህ ታሪክ ባለቤት በርታ አምላክ ላንተ ያዘጋጀልህ ይኖራልና ተስፋ አትቁረጥ :: ለነገሩ ከቄስ ተጠግተሃል በቅርብ ቀን ደጉ ሳምራዊ መጨረሻህን እንደሚያሳውቀን ተስፋ አለኝ ::

    ReplyDelete
  4. Well, first I want say sorry to the person with the story for his love hurt. But as much as the girl he fall in love with over Facebook was not faithfull enough both for him and her family at home, she was atleast fothcoming in disapproving his vist to her. To me, the rest he did it himself. As a culture we Ethiopians have this problem of not taking what people told as at face value. This brother forexample if he just honer her refusal to his visit (even though she lied him about her reason to refuse) he would save himself a disappointment that may not go away for a while.

    ReplyDelete
  5. nice view and interesting . kesisi God bless u

    ReplyDelete
  6. ጥሩና አስተማሪ ነው:: ቀሲስ ይበርቱ : በተገኘው መንገድ ሁሉ ማስተማሩና መምከሩ ተገቢ ነው:: ይበል ብለናል

    ኃይለ ገብርኤል ከሰሜን ሲያትል

    ReplyDelete
  7. betam astemari new khy !!!

    ReplyDelete
  8. ሴትዮዋ ያደረጉት ነገር አግባባ ያለው አለመሆኑ ግልጽ ነው። የሚገርመው ግን ከሴትዮዋ ፈቃድ ውጭ ከአሜሪካ ተነስቶ የሄደው የዋሁ ሰው ነው። ይህ ለነገሩ የዋህነት ሳይሆን ሞኝነት ነው። የምን መጃጃል ነው? ሲበዛም ደስ አይልም።
    ቀሲስ ይበርቱልን ጥሩ ዘግበዋል። አስተማሪም ነው።

    ReplyDelete
  9. ታሪኩ የብዙዎች ነው ፡ ክቡር የሆነውን ፍላጎታቸውን በራሳቸው ዛቢያ ብቻ በመሸከርከር ከስሜት ባልራቀ በብልህነት አጦት የሆነ ነገራቸውን ተስፋ በማድግ ተፈጻሚነት ሲጎድላቸው ህይዎታቸውን በሙሉ በጥርጣሬ እንዲኖሩ ለሚይጋበዙት፤ እንዲሁም ንፁህ ህሊናቸውን በማስመሰል ፡ በውሸት አደፍርሰው ለጥቅም ብቻ ለሚኖሩ ሰዎች ታሪኩ አስተማሪ ነው፡፡

    ReplyDelete
  10. I think , it's a great lesson, for all of us, specially for diaspora, who believe z photograph.Using Technology has pros & Cons. I wish our (Ethiopian females) to be as our mothers, the one who were confident with what they have, Honest to their husbands, their culture.... May God help us to be wise... Thank U Kesis for ur lesson

    ReplyDelete
  11. http://debelo.org/

    http://www.zeorthodox.org/

    http://www.melakuezezew.info/

    http://www.kesisyaredgebremedhin.com/

    http://www.adebabay.com/

    http://www.betedejene.org/

    http://www.aleqayalewtamiru.org/

    http://www.mahletzesolomon.com/

    http://degusamrawi.blogspot.com


    http://www.tewahedomedia.org

    http://www.eotc-mkidusan.org/site/

    http://suscopts.org/

    http://www.dejeselam.org/

    http://mosc.in/

    ReplyDelete
  12. kemer !Gin lemen yewashal ?? khy !!

    ReplyDelete
  13. betam tiru ena astemari new gin ena yemigeremeg sew bedenb sayitewaweki endat leteleki neger yitesasebale degmos tegebim ayidelem ayidelem be facebook awkehat endihum kebedowale zemenu eko

    ReplyDelete
  14. በጣም ዘግይቼ ይህን ብሎግ በማወቄ አዝናልሁ፡፡ኢትዮጵያ ያሉ ብቻ አይደሉም ውጭ ያሉ ኢትዮጵያውያንም በጣም ውሸታም ናቸው መንፈሳዊ ሲያገኙ መንፈሳዊ አለማዊ ሲያገኙ አለማዊ እየመሰሉ ብዙ ቃል እየገቡና ተስፋ እየሰጡ የሰውን ህይወት ሚበጠብጡ
    እኔ ካላሁት ክልል የሄደና በአሜሪካ በአንዱ ስቴት የሚኖር ሰው ባጋጣሚ በፌስ ቡክ ተዋውቀን ስለ ሃገራችን ስለቤተክርስትን መረጃ እንለዋወጥ ነበር ፡፡ሲውል ሲያድር ጓደኛ መሆን እንደምንችል ጠየቀኝ እኔም ምንም ጓደኛ ስላልነበረኝ ተስማማን ለ5 ወራትም ቆየን ይደውልልኛል ኦን ላይን ስንገናኝም እናወራለን እስከዚ ድረስ ግን እራሱን እንደመንፈሳዊ ነበረ ሚደርገው በርግጥም መንፈሳዊ ነው ግን አ.አ ሌላ ብዙ ቃል የገባላት ልጅ አለች በኃላ ለኔ የፃፈውን ሚሴጅ ለስዋ ላከላት ልጅትዋም ስሜን አይታ አድ አደረገችኝ ሁሉንም ተነጋገርን ከልጅትዋ ጋር እኔም ለሱ ሁሉኒመ አስረድቸው ተለየሁት ከስዋም ጋር ተለያየ ፡፡ስለዚህ ሁሉም ዋሾ ሆኗል
    ፊቅርተማርያም
    ከአዋሳ

    ReplyDelete
  15. Cool and that i have a tremendous give: Where To Remodel House home renovation victoria

    ReplyDelete