Friday, May 27, 2011

አባቶቻቻን ይታረቁ !!! ክፍል ፪

ክፍል ፪


የኢትዮጵያ ሲኖዶስ

አገራችን ኢትዮጵያ አፍሪካ ካሏት አገሮች አንዷ ስትሆን አውሮፓውያን አገራትን እንደ ቅርጫ ሥጋ ተቀራምተው ቅኝ ሲገዙ ያልተገዛችና የነጻነት ተምሳሌት ሁና በመኖሯ ስሟ በዓለም ጎልቶ የሚነገርላት ናት :: ይህ ብቻ ሳይሆን አስቀድማ ብሉይን በኋላም አዲስ ኪዳንን ተቀብላ የኖረች አገር በመሆኗ አገረ እግዚአብሔር በመባል ትታወቃለች :: እንግዳ ተቀባይና ሰው አክባሪነቷም ሌላው መለያዋ ነው :: ሌሎች ጎረቤት አገሮች የራሳቸውን ቋንቋ ባህል ሃይማኖት ሲያጡ ባህሏን ታሪኳንና ማንነቷን ጠብቃ የኖረች የራሷ ቋንቋ ከነፊደሉ ፣ሥነ ጹሑፍ ፣ኪነ ጥበብ እና ሥነ ጥበብ ያላት እንዲሁም ታሪካዊና ጥንታዊ ቅርሶች ያላት መሆኗ ለአፍሪካ ኩራት እንድትሆን አድርጓታል ::

ለኢትዮጵያ ከላይ ለተዘረዘሩትና ላልተገለጹ ማንነቷ ምክንያት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቶያን መሆኗ የሚያነጋግር አይደለም :: ቤተ ክርስቲያኗ ተከታዮቿን በሥነ ምግባር አንጻ ለእግዚአብሔር መንግሥት ዝግጁ ማድረግ ብቻ ሳይሆን ዜጎች ለአገርና ለወገን የሚታመኑ ሰላማዊና አምራች እንዲሆኑ ከፍተኛ አስተዋጽኦ የምታደርግ ናት::

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሰላምን የምትሰብክ ፣ ስለ ሰላም የምትዘምር ፣ ልዩነትን የምትጸየፍ ና የተጣላ የምታስታርቅ ስትሆን መሪዎቿም ይህን የሚያስፈጽሙ የሰላም መልእክተኞችና የፍቅር አስተማሪዎች ሊሆኑ የግድነው :: ትክክለኛ ገጽታዋ ይህ ሁኖ ሳለ ዛሬ በቤተ ክርስቲያን አባቶች መካከል የሚታየው ልዩነት የቤተ ክርስቲያኗን ስምና ታሪክ የሚያበላሽ ሁኖ ይገኛል :: በ፲፻፱፻፹፫ ዓ.ም የደርግ መንግሥትን መውደቅ ተከትሎ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፬ኛ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ እንድዲሁም ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ ፣ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ እና ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ከአገር መሰደድ ምክንያት ቤተ ክርስቲያን ከሁለት ተከፍላ በአባቶች መወጋገዝም ምዕመናን ግራ ተጋብተውና የሚያደርጉት ጠፍቶባቸው በቤተ ክርስቲያኗ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ጥፋት በቤተ ክርስቲያን በራሷ ልጅወች እየተፈጸመ ይገኛል::

ስደተኛው ሲኖዶስ
             ዛሬ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የኢትዮጵያ ሲኖዶስ ፣ስደተኛ ሲኖዶስ እና ገለልተኛ በሚል ተከፋፍላ ያለችሲሆን በየአጥቢያው ያለው አለመግባባትና ፍቅር መጥፋት ሳቢያ ወደ ሁሉም አንሄድም ብለው የተቀመጡትን ቤት ይቁጠራቸው ::የቀደሙት አባቶቻችን ደክመው ያሰባሰቡት ምዕመን ጠባቂ አጥቶ ሲበታተንና ወደሌላ በረት ሲገባ ከማየት የበለጠ ምን የሚያሰቅቅ ነገር አለ ?

ከቀን ቀን ልዩነት እየሰፋ ችግሮች እየተባባሱ መሆኑ የቤተ ክርስቲያኗን ልጅዎች እጅግ እያሳዘነና እያስለቀሰ ይገኛል ::

አባቶች መምህራነ ፍቅር እንደመሆናቸው ልዩነታቸውን በመነጋገር ፈትተው ሥልጣንን ዝናን ክብርን ሳያስቡ ላስተማረችና ለዚህ ደረጃ ላደረሰች ቤተ ክርስቲያን ይልቁንም ከእግዚአብሔር ለተቀበሉት አደራ ቅድሚያ በመስጠት ቤተ ክርስቲያንን አንድ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ::

አባቶች ሰላም ለመፍጠር ፈቃደኛ ካልሆኑ ፣ ለመንጋው የማይራሩ ፣ የህዝብ ሀዘን የማይሰማቸው እና የነገዋ ቤተ ክርስቲያን የተበታተነችና ጉልበት የሌላት እንድትሆን ካደረጉ እግዚአብሔርም ታሪክም ይጠይቃቸዋል :: ልዩነት ተወግዶ ለቤተ ክርስቲያን አንድነት ሲባል አባቶቻችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መስማማት አለባቸው ::

አሁን ያለውን ዝርዝር ችግርና የመፍትሔ ሃሳብ ከመሰንዘሬና ለውይይት ከማቅረቤ በፊት ስለ ኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አባቶች ሹመት ታሪክ ጥቂት ነጥቦችን ለማንሣት እሞክራለሁ ::

ቤተ ክርስቲያናችን ክርስትናን በመጀመር ቀዳሚውን ስፍራ ብትይዝም ከራሷ ልጅዎች ጳጳስ መሾም ከጀመረች ገና የአንድ ጎልማሳ እድሜ ብቻ ነው ያስቆጠረች ::

የምስራቅ አብያተ ክርስቲያናት/ Oriental churches / ከሚባሉት ግብጽ ፣አርመን ፣ሦርያና ሕንድ ጋር አንድ ዓይነት ዶግማና ቀኖና ያላት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በ፴፬ ዓም በጃንደረባው አማካኝነት ክርስትናን ተቀብላ ለ፪ሺ ዓመታት ስትሰብክ የኖረች ጥንታዊት ቤተ ክርስቲያን ናት ::

የኢትዮጵያውያን ጳጳሳት ሹመት አጀማመር

የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ለ፩ሺ፮፻ ዓመታት በርካታ ገንዘብና ወርቅ ለግብጽ ቤተ ክርስቲያን በመገበር ጳጳሳትን ስታስመጣ ኑራለች :: ለዚህ ምክንያቱ ምን እንደሆነ ብፁዕ አቡነ ጎርጎሪዎስ “የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ” በሚለው መጽሐፋቸው ሲገልጡ በጉባኤ ኒቅያ ቀኖና አንቀጽ ፵፪ በስርዋጽ የገባ “ኢትዮጵያውያን ከሊቃውንቶቻቸው ጳጳስ አይሹሙ “ የሚል ትዕዛዝ ነበር :: ይህ በሰባተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተጨመረ ነው ይላሉ :: በዚህ ቀንበር ማጥበቂያ ተብሎ በሚታወቀው አንቀጽ ምክንያት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በራሷ ልጅወች እንዳትመራ ተደርጎ ለቁጥር የሚያታክቱ ዓመታት ኑራለች ::
በንጉሥ ሐርቤ

ቤተ ክርስቲያኗ በራሷ ቋንቋ የሚያስተምሩ ከራሷ የተገኙ አባቶች ሊሾምላት እንደሚገባ በሊቃውንቱ በተለያዩ ዘመናት ሲጠይቁ ኑረዋል :: ይልቁንም በ፲፩ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ነግሦ የነበረው ሐርቤ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ከኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ጳጳሳት እንዲሾምላት ለማድረግ ያደረገው ጥረት ከፍተኛ በመሆኑ ታሪክ ሲያስታውሰው ይኖራል ::

በ፲፫ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ተከስቶ በነበረ የመስቀል ጦርነት የተነሣ የግብጽና የኢትዮጵያ ግንኙነት በመቋረጡ ምክንያትና ኢትዮጵያ ያለ ጳጳስ በመቆየቷ ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ተሰብስበው በወቅቱ የደብረ ሊባኖስ እጨጌ የነበሩትን ኢትዮጵያዊ አቡነ ተክለ ሃይማኖት በመንበረ ጵጵስናው እንዲቀመጡ ካደረጉ በኋላ እርሳቸውም ዲቁናና ቅስና በመስጠት አገልግሎቱ እንዳይቋረጥ ተደርጓል ::

ጦርነቱ እንደተጠናቀቀ የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ስድስተኛውን ጳጳስ ወደ ኢትዮጵያ ልካለች በዚህ ጊዜ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሥልጣኔን አልለቅም አላሉም :: ይልቁንም በአገልግሎት በቆዩበት ጊዜ ኢትዮጵያውያን ለኃላፊነት የሚበቁ ውጤታማ ጠንካራ መሆናቸውን ባፈሩት ፍሬ ባከናወኑት ተግባር አስመስክረው መንበሩን ከግብጽ ለመጡት አባት አስረክበዋል ::



አጼ ዮሓንስ

በ፲፱ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አስቀድሞ በተደጋጋሚ ሲቀርብ የቆየውንና በግብጽ ቤተ ክርስቲያን ምላሽ ተነፍጎት የቆየውን ከኢትዮጵያውያን ሊቃውንት አባቶች ይሾሙልን ጥያቄ ዓፄ ዮሓንስ አጠናክረው ጠየቁ ምላሹ ግን አንድ ግብጻዊ ጳጳስ የነበሩትን ሦስት አባቶች በመጨመር በ፩፰፻፸፬ ዓ.ም ግብጻውያኑን አቡነ ጴጥሮስ የኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ፣ አቡነ ማቴዎስ የሸዋ ኤጲስ ቆጶስ ፣አቡነ ሉቃስ የጎጃም ኤጲስ ቆጶስ እና አቡነ ማርቆስ የበጌምድር ኤጲስ ቆጶስ ሁነው ተሹመዋል :: አቡነ ጴጥሮስ ሲያርፉ የሸዋ ኤጲስ ቆጶስ የነበሩት አቡነ ማቴዎስ መንበረ ጵጵስናውን ይዘው በሸዋ ኤጲስ ቆጶስ ሁነው ለ ፰ ዓመታት በኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስነት ለ ፴፯ ዓመታት አገልግለዋል ::
                                                 


ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ
                                                      በንግሥተ ነገሥታት ዘመነ መንግሥት ኢትዮጵያውያን መልስ አጥተውበት የኖሩትን ጳጳስ ከራሳችን ወገን ይሾምልን ጥያቄ በሊቃውንቱ አማካኝነት በወቅቱ በነበሩ መገናኛ ብዙሓን /በጋዜጣ/ ሲወጣ ኅሳቡ ወደ ቤተ መንግሥት ደረሰ በዚህ ምክንያት ጉዳዩ ከቤተ ክህነት አልፎ የቤተ መንግሥት ሆነ :: በዘመኑ አልጋ ወራሽና ባለ ሙሉ ሥልጣን እንደራሴ የነበሩት ራስ ተፈሪ መኰንን ከንግሥተ ነገሥት ዘውዲቱ ፣ ከመሣፍንቱ ፣ ከመኳንንቱ እና ከሊቃውንቱ ጋር በመሆን ተፈጻሚ የሚሆንበትን ሁኔታ መከሩ ::
ልዑል አልጋወራሽም ባረፉት የኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ምትክ ሌላ እንዲመደቡና ከእሳቸውም ጋር በኢትዮጵያ ወንጌል እንዲስፋፋ በርከት ያሉ ኢትዮጵያውያን ጳጳሳት እንዲሾምላቸው በመጠየቅ በወቅቱ የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ለነበሩት ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቄርሎስ አምስተኛ ደብዳቤ ላኩ ::





ፓትርያርኩም ደብዳቤው ደርሷቸው ከተመለከቱት በኋላ የሚከተለውን ምላሽ ሰጡ ::

“ጉዳዩን ብቻየን ለመወሰን ስለማልችል በጉዳዩ ላይ የሚመክር ጉባኤ ጠርቼ እወያይበታለሁ “ ይህን ምላሽ ያገኙት ልዑል አልጋ ወራሽ ተፈሪ መኰንንና የኢትዮጵያውያ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትም ውሳኔውን እየተጠባበቁ እያለ የግብጽን ቤተ ክርስቲያን ለ ፶፪ ዓመታት ከ፱ ወራት የመሩት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቄርሎስ ማረፋቸው ስለተሰማ ረፍታቸውን ምክንያት በማድረግ አልጋ ወራሽ የሃዘን መግለጫ ላኩ :: ከዚህ ላይ የፓትርያርኩ ረፍት ተሰምቶ የሃዘን መግለጫው ሲላክ የኢትዮጵያውያን ጥያቄ ምልስ እንዲያገኝ አዲስ አበባ ላይ ሰባት ጊዜ መድፍ ተተኩሷል ::

አሁንም ፓትርያርኩን የሚተካ እስኪመረጥ ድረስ የኢትዮጵያውያኑ ጥያቄ መልስ ሳያገኝ ቆይቶ ታህሳስ ፯ ቀን ፲፱፻፳፩ ዓ.ም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ዮሓንስ ፲፱ኛው የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ሁነው እንደተሾሙ ለልዑል አልጋወራሽ ተፈሪ መኮነን ተገለጸላቸው :: አልጋወራሹም የተሰማቸውን ደስታ ለአዲሱ ፓትርያርክና ለግብፅ ቤተ ክርስቲያን ሲልኩ አያይዘው ከአሁን ቀደም የጠየቁት ከኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ጳጳስ ይሾምልን ጥያቄ አፋጣኝ መልስ እንዲያገኝ አሳስበው በአቡነ ማቴዎስ ምትክ አንድ ሊቀ ጳጳስ ተሹሞ እንዲላክ እርሱም አዲስ አበባ ሲደርስ ከኢትዮጵያውያን እየመረጠ ጳጳሳትን እንዲሾም የሚል ጥያቄ ያዘለ መልዕክት ላኩ ::
አጼ ኃይለ ሥላሴ

አዲሱ የእስክንድርያ ፓትርያርክ ጥያቄውን ሙሉ በሙሉ ባለመቀበል አንድ ግብጻዊ ሊቀ ጳጳስ ብቻ ለመመደብ መፍቀዳቸውንና ሊቀ ጳጳሱ ከኢትዮጵያውያን ለመሾም ቀኖናው እንደማይፈቅድላቸው በመግለጥ ጳጳስ ተብለው እንዲሾሙ ብፁዕ እጨጌን እንዲላኩላቸውና ከሊቀ ጳጳሱ ጋር በኢትዮጵያ በየክፍሉ የሚራዱ ሁለት ግብጻውያን ጳጳሳት እንደሚመድቡ ምላሽ ሰጡ ::

ዲ/ን መርሻ አለኽኝ “ ዜና ጳጳሳት ኢትዮጵያውያን “ በሚል በ፲፻፱፻፺፯ ዓ.ም ባሳተሙት መጽሐፍ እንደገለጹት አልጋ ወራሽ ይህ መልዕክት እንደደረሳቸው የሚከተለውን ሌላ ደብዳቤ ላኩላቸው ፡

ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ዮሓንስ አንድ ሊቀጳጳስ ለመሾም ከእኛም ለአንዱ እጨጌ ጵጵስና ለመስጠት መፍቀድዎን የሚገልጽ መልዕክትዎ ደርሶን ተመልክተነዋል ይሁንና እንዳሰብነው የትምህርት ችግራችንን የሚያቃልል አይደለም የሚጨመሩትም ሁለት ግብጾች ቋንቋችንን ስለማያውቁት ፈቃድዎ ሁኖ በቋንቋችን የሚያስተምሩ ሊቃውንት የሚያስፈልገንን ያህል ከመልዕክተኞቻችን ጋር ወደ እናንተ ልከን እንዲሾሙ ቢደረግ ይህ ካልሆነም የኛን ሊቃውንት ጳጳስ አድርገው ሹመው ከግብጽ የሚመደቡት ሊቀ ጳጳስ ጋር ቢልኩልን ሁለተኛው ኃሳብ ግን እስከ አሁን ጸንቶ የኖረው የአባትና የልጅነት መተማመን እንዳይጎድል እንጅ ኃሳባችን አሁንም የመጀመሪያው መሆኑን ያውቁልን ዘንድ እንለምንዎታለን ::

ልዑሉ መልዕክቱን ከላኩ በኋላ ጉዳዩ እልባት እንዲያገኝ ግብፅም ትኩረት እንድትሰጠው በወቅቱ የትምህርት ሚ/ር ዳይሬክተር በነበሩት በአቶ ሳህሌ ጸዳሉ የሚመራ ልዑክ ወደ ግብፅ ላኩ ልዑካኑም ከፓትርያርኩ ጋር ጠንከር ያለ ውይይትና ክርክር አድርገዋል ፓትርያርኩም አስቸኳይ የሲኖዶስ ስብሰባ ጠርተው ከተነጋገሩ በኋላ አንድ ግብጻዊ ሊቀ ጳጳሳት ከአምስት ኢትዮጵያውያን ጳጳሳት ጋር እንዲሾሙ ፈቀዱ ::

ይህ ውሳኔም ለግርማዊ ንጉሥ ተፈሪ መኰንን በቴሌግራም እንዲተላለፍ ተደረገ :: መልዕክቱም

“ ሐዋርያዊ ቡራኬያችን ለግርማዊነትዎ ይሁን ከኢትዮጵያ መምህራን አምስት ሰዎች ተመርጠው ጳጳሳት ሁነው አምስት የኢትዮጵያ ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት እንዲሾሙ ፈቅደናልና አምስት መነኮሳት እንዲልኩልን እንለምናለን “

ልዑል አልጋ ወራሽም ባስቸኳይ የሚከተለውን ምላሽ ሰጥተዋል :

“በሣህሌ ጸዳሉ በኩል ላስታወቅንዎ ጉዳይ ከቡራኬዎ ጋር በላኩልን ምላሽ ደስ ብሎናል መነኮሳቱንም እንደሚያስፈልግ አድርገን እንልካለን :: እግዚአብሔር ቅዱስነትዎን ይጠብቅ ::”

ይቀጥላል



12 comments:

  1. ቃለ ሕይወት ያሰማልን ከሲስ መልካም ጥረት ነው.እግዚአብሄር ለአባቶች ልቦና ሰጥቶ ዲያብሎስን አሳፍሮ ቤተ ክርስቲያናችንን ይጤብቅልን.ምንም እንኩዋን ቤ/ክ ያለፈተና ባትኖርም ይሄ በራስ መፈተን ግን ከበድ ያለ ነዉ .

    ReplyDelete
  2. let us say The current pop moved europ due to because E.p.r.d.f left the chair , Do not you think the Abunu paulos will have the 3Rd Senyodys????????????

    ReplyDelete
  3. ... እኔ የጳውሎስ ነኝ፤ እኔ ግን የኬፋ ነኝ፤ እኔስ የክርስቶስ ነኝ ትላላችሁ። ክርስቶስ ተከፍሏልን ?...“ 1ኛ ቆሮ 112-13

    ReplyDelete
  4. እግዚአብሔር ይመስገን በዚህ መልክ የተዘጋጀ ዌብ ሳይት እስካሁን አላየሁም ጥሩ መረጃ ነው ያገኘነው :: የማናውቀውን ታሪክ ስላሳወቃችሁን እናመሰግናለን እውነትም ደጉ ሳምራዊ ::እባካችሁ የመወያያ ነጥቡን ቶሎ አሳውቁንና እንተንፍስበት ........

    ReplyDelete
  5. ይታረቁ ወይንስ ይታነቁ ?ወስዳችሁ ለወያኔ ልታስረክቡ ? ሞኛችሁን ፈልጉ ::

    ReplyDelete
  6. ስለ እግዚአብሐር ብላችሁ ሁሉን ነገር ወደ ፖለቲካ አትውሰዱት :: ለምንድን ነው ቤተ ክርስቲያን አንድ እንድትሆን የማንጥረው ?ጠርጣራው ከአስተያየትህ እንደተረዳሁት ፖለቲከኛ ትመስላለህ የቀረበው ፁሁፍ የሃይማኖት ስለሆነ የፖለቲካ ሲጻፍ እንጠራሃለንና ይህን መድረክ ለቀቅ አርገው:: እናንተ ደጉሳምራዊ አዘጋጅወች ኃሳባችሁ ትክክለኛ ምልእክት ማስተላለፍ ከሆነ ለምንድን ነው መንፈሳዊነት የሌላቸው አስተያየቶች እንዲወጡ የምታደርጉት

    ReplyDelete
  7. ጹሑፉ ክርስትና ይነሳ ?

    ReplyDelete
  8. የሚገርም ጽሁፍ ነው ምክንያቱም የሀገራችን ታሪክ 1ኛበመደገፍ 2ኛበመቃወም የሚጻፍ በመሆኑ ለአንባቢያን ያስቸግራል ይህ ጽሁፍ ከጅምሩ በጣም ግሩም የሆነ አቀራረብ ነው ከክፉ መካሪ ይሰውረው በእውነት እንደ ጀመረ በእውነት ያስጨርሰው በእርግጥ እውነት መራር ናት የተጎነጫት ግን ከሆድ ህመም ትፈውሳለች ሁላችን እንጠጣት እንድንፈዎስ

    ReplyDelete
  9. selam kesis
    semonun eyasebkut yake neger new yawetut. yebetechristian tarikachinin saizaba mawek ,lemekorkor yitekmaldegmomlewedefit tarik
    new silebizu neger endilun,tesatafiwochim yalachewin biwerewiru ,be misil ,betsihuf,be audio,be videoendih tarikmaskemet new.

    ReplyDelete
  10. useful websites

    http://www.mahletzesolomon.com/
    http://www.zeorthodox.org/
    http://www.dejeselam.org
    http://www.kesisyaredgebremedhin.com
    http://www.betedejene.org
    http://www.eotc-mkidusan.org/site/
    http://www.danielkibret.com/

    ReplyDelete
  11. This is good,but it should be genuine. What makes the problem more complex is instead of working to solve the problem on the part of yehager betu sinodos degafiwochina papasat, they engagged in dividing churches establishing more. This never solves the problem. It is just fullfiling the political mission to weaken the oppostion.They do not care about the church or the country.Is npt mentioning aba paulos's name wron? looking at what he has done to the church and his disobeying the synod's decision, Ithinh every church need to stop mentionong his name. That does not make a church to be called geleltegna or under EOTC!The right approach is to not mention their name unless they come to terms.

    ReplyDelete