Friday, October 19, 2012

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ኮሜቴ መግለጫ


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አባቶች መካከል ላለፉት ሃያ ዓመታት ተፈጥሮ የቆየውን ልዩነት ለመፍታት ከሁለት ዓመታት በላይ ሲንቀሳቀስ የቆየው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ በኢትዮጵያ እና በውጪው ዓለም ለሚገኙ አባቶች ጠንከር ያለ ተማጽኖ ያለበት መግለጫ ያወጣ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስትም በቤተ ክርስቲያኗ የሰላምና የዕርቅ ሂደት ምንም ዐይነት ጣልቃገብነት ባለማሳየት የተጀመረው ሰላም ከፍጻሜ እንዲደርስ ትብብር እንዲያደርግ ጠይቋል::

 

በተያያዘ ዜና በሰሜን አሜሪካ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት /ቤቶች አንድነት ጉባኤ የቤተ ክርስቲያን አንድነትን በማስመልከት መግለጫ አውጥቷል::  የአባቶቻችን ትእዛዝ መፈጸም እና ለተጀመረው እርቀ ሰላም መሳካት የልጅነት ድርሻችንን መወጣት መንፈሳዊ ግዴታችን ነው በማለት የሰላምና አንድነት ጉባኤው የሚያደርገው እንቅስቃሴ ለመደገፍ መዘጋጀቱን ገልጿል::

 

ከጥቅምት አስራ ሁለት ጀምሮ የሚካሄደው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የተፈጠረው ልዩነት ተወግዶ ቤተ ክርስቲያኗ አንድ እንድትሆን እንዲያደርግ ከመላው ዓለም በሚገዩ ክርስቲያኖች፣ማኅበራት እና ልዩ ልዩ ተቋማት ብሎም የቤተ ክርስቱያን ወዳጅዎች ግፊት እየተደረገበት ይገኛል::   

እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያናችንን አንድ ያድርግልን!

No comments:

Post a Comment