Friday, October 19, 2012

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ኮሜቴ መግለጫ


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አባቶች መካከል ላለፉት ሃያ ዓመታት ተፈጥሮ የቆየውን ልዩነት ለመፍታት ከሁለት ዓመታት በላይ ሲንቀሳቀስ የቆየው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ በኢትዮጵያ እና በውጪው ዓለም ለሚገኙ አባቶች ጠንከር ያለ ተማጽኖ ያለበት መግለጫ ያወጣ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስትም በቤተ ክርስቲያኗ የሰላምና የዕርቅ ሂደት ምንም ዐይነት ጣልቃገብነት ባለማሳየት የተጀመረው ሰላም ከፍጻሜ እንዲደርስ ትብብር እንዲያደርግ ጠይቋል::

 

በተያያዘ ዜና በሰሜን አሜሪካ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት /ቤቶች አንድነት ጉባኤ የቤተ ክርስቲያን አንድነትን በማስመልከት መግለጫ አውጥቷል::  የአባቶቻችን ትእዛዝ መፈጸም እና ለተጀመረው እርቀ ሰላም መሳካት የልጅነት ድርሻችንን መወጣት መንፈሳዊ ግዴታችን ነው በማለት የሰላምና አንድነት ጉባኤው የሚያደርገው እንቅስቃሴ ለመደገፍ መዘጋጀቱን ገልጿል::

 

ከጥቅምት አስራ ሁለት ጀምሮ የሚካሄደው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የተፈጠረው ልዩነት ተወግዶ ቤተ ክርስቲያኗ አንድ እንድትሆን እንዲያደርግ ከመላው ዓለም በሚገዩ ክርስቲያኖች፣ማኅበራት እና ልዩ ልዩ ተቋማት ብሎም የቤተ ክርስቱያን ወዳጅዎች ግፊት እየተደረገበት ይገኛል::   

እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያናችንን አንድ ያድርግልን!

Saturday, August 18, 2012

      

  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አምስተኛ ፓትርያርክ ዕረፍተ ሞትን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ የተሰጠ የሃዘን መግለጫ : 
                                                                                  

                                                                                                                                                   ነሐሴ 11/2004 ዓ/ም    
Aug 17/2012
   
    “ክቡር ሞቱ ለጻድቅ በቅድመ እግዚአብሔር” (መዝ 115፥6)
የአምስተኛውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ  የብፁዕ ወቅዱስ ዶ/ር አቡነ ጳውሎስን ዕረፍት አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን  የሰላምና አንድነት ጉባኤ ጽ/ቤት የተሰጠ የኃዘን መግለጫ።
ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ
አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ
እንዲሁም በቅድስት ሀገር ኢትዮጵያና በመላው ዓለም ለሚኖሩ የኢትጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናትና ምዕመናን በሙሉ።
          በሰሜን አሜሪካ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ በአምስተኛው ፓትርያርክ በብፁዕ ወቅዱስ ዶ/ር አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ፤ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፤ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም፤ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዝዳንትና የዓለም የሰላም አምባሳደር ድንገተኛ ዕረፍት ምክንያት የተሰማውን ከፍተኛና ትልቅ ኃዘን ይገልጻል። እንደሚታወቀው ቅዱስነታቸው   ለቤተ ክርስቲያናችን ዕድገትና መሻሻል፣ መጠናከርና መስፋፋት የሚጠቅሙ በርካታ መንፈሳዊ ተግባራትን ያከናወኑ  ታላቅ የቤተ ክርስቲያናችን አባትና  የሥራ ሰው ነበሩ። በመሆኑም ቅዱስነታቸው በአገልግሎት ዘመናቸው ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ያከናወኗቸው ዘርፈ ብዙ ሐዋርያዊ ተግባራት ምን ጊዜም ሕያውነታቸውን ሲያስታውሱ ይኖራሉ። ቅዱስነታቸው ብሔራዊውን የአብነት ትምህርትና ዘመናዊውን ዕውቀት አገናዝበው የተማሩ ታላቅ ሊቅ ስለነበሩ ለቤተ ክርስቲያን እጅግ አስፈላጊ ቅዱስ አባት ነበሩ፤ ይልቁንም ባለንበት ዘመን ቤተ ክርስቲያናችንን በዓለም መድረክ ወክለው ያከናወኗቸው ብዙ ሥራዎች ዘወትር ሲታሰቡ ይኖራሉ። ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን እኒህን ታላቅ አባት በድንገት በማጣቷ ልባዊ ኃዘናችንን በድጋሚ እንገልጻለን። በእውነቱ የቅዱስነታቸው  ድንገተኛ ዜና ዕረፍት ለቤተ ክርስቲያን ትልቅ  ኃዘን ነው።
          ይልቁንም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ በቅዱስነታቸው አባታዊ ቡራኬና በቅዱስነታቸው በሚመራው ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መልካም ፈቃድ ሦስተኛውን ዙር የሰላምና አንድነት ጉባኤ ለማካሄድ በዝግጅት ላይ ሳለ ይህንን ቤተ ክርስቲያንን አንድ የሚያደርግ ታሪካዊ ሒደት ለፍጻሜ ሳይበቃ የቅዱስነታቸው ዜና ዕረፍት መስማቱ ጉባኤውን በእጅጉ አሳዝኖታል፤ ሊያስከትል የሚችለው ውጣ ውረድም ከወዲሁ አሳስቦታል። ቅዱስነታቸው የጀመሩትን የቤተ ክርስቲያን ሰላምና አንድነት ጥረት የመጨረሻ ፍሬ ሳያዩ በድንገት በማለፋቸው ኃዘናችን ወሰን የለውም። የሰላምና አንድነት ጉባኤው በቅዱስነታቸው የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ ተገኝተው የጉባኤውን የኃዘን መግለጫ የሚያደርሱ ልዑካንን  ሰይሞ ለመላክ በአንድነት ወስኗል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ ቤተ ክርስቲያንን አሁን ካለችበት አሳሳቢ የልዩነት ፈተና ይበልጥ ወደ ባሰና ወደ ከፋ ችግር እንዳትሄድ ቅዱስ ሲኖዶስ የቤተ ክርስቲያንን አንድነት ተቀዳሚ ሥራው በማድረግ ለዘመናት በአንድነቷ ጽንታ የኖረችውን ቤተ ክርስቲያን የቀድሞ ታሪኳን ለመመለስና ለማደስ ተገቢውን ሥራ በአንድነት እንዲሠራና እስካሁን ድረስ የቆየው የልዩነት ምዕራፍ እንዲዘጋ፣ በቅዱስነታቸውና በቅዱስ ሲኖዶስ በጎ ፈቃድ የተጀመረውን የሰላምና አንድነት ሒደትም ለፍሬ ያበቃው ዘንድ ጉባኤው ከታላቅ አደራ ጋር ይማጸናል።
በመሆኑም የሰላምና አንድነት ጉባኤው ለቅዱስ ሲኖዶስና ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መላው ካህናትና ምእመናን ወምእመናት ከዚህ የሚከተለውን መልእክት ያስተላልፋል።
1ኛ/ በቅዱስነታቸው ድንገተኛ ዕረፍት ምክንያት የተሰማንን ጽኑ ኃዘን እየገለጽን ከምንም በላይ በቅዱስ ሲኖዶስ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባው ዋነኛውና አንገብጋቢው ጉዳይ ቤተ ክርስቲያንን አንድ ማድረግ መሆኑን በአጽንኦት እንገልጻለን፤  እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ ባለፈው ሐምሌ ወር ሦስተኛውን ጉባኤ አበው ለማካሄድ ተገቢውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ላይ ነበር። ይሁን እንጂ በግንቦቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ የላክነው ደብዳቤና ባለ ሰባት ነጥብ የመፍትሔ ሐሳቦች በአገር ውስጥና በውጭው ዓለም የሚገኙት አባቶቻችን በዕርቀ ሰላም ውይይቱ ላይ ለመገኘት ሙሉ ፈቃዳቸው መሆኑን ገልጸውልን ነበር። በዚህ መካከል ግን በአዲስ አበባ በኩል በሰላምና አንድነት ጉባኤው የቀረቡትን ሰባቱን የመፍትሔ ሐሳቦች አስመልክቶ ቅዱስ ሲኖዶስ በወርኃ ሐምሌ መግቢያ ላይ ተነገጋሮባቸው በአፋጣኝ መልስ እንደሚሰጠን በደብዳቤ ተገልጦልን ነበር። ያንን መልካም ዜና በጉጉት እየተጠባበቅን ሳለን ይህ ድንገተኛ ኃዘን ቤተ ክርስቲያንን ገጠማት፤ አሁንም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ ሦስተኛውን የዕርቀ ሰላም ውይይት በወርኃ ጥቅምት ከሚካሔደው ዓመታዊው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በፊት ለማካሔድ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ላይ ነው። በመሆኑም በመላው ዓለም የተበተነችውን ቤተ ክርስቲያን አንድ ለማድረግ፣ በሀገር ውስጥና በሀገር ውጭ የሚገኙት አባቶችም በቅርቡ በሚዘጋጀው የሰላምና አንድነት መድረክ ተገናኝተው ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላምና አንድነት ተነጋግረው፣ ችግሩን በውይይት በመፍታት ቤተ ክርስቲያንን አንድ ያደርጓት ዘንድ ጥሪውን ያቀርባል።  

2ኛ/ ቤተ ክርስቲያን ለወደፊቱ ተለያይታ እንዳትቀር በሀገር ውጭና ከሀገር ውስጥ ባሉት አባቶች መካከል ያለው ልዩነት በአንድነት ሳይፈታ ሌላ ፓትርያርክ የመተካቱን ጉዳይ ቅዱስ ሲኖዶስ ከወዲሁ በከፍተኛ አትኩሮት እንዲያስብበት፤ ይልቁንም የቤተ ክርስቲያንን ሰላምና አንድነት በማጽት የቀድሞውን የአንድነት ታሪክ ይመልሱት ዘንድ ጉባኤው በቤተ ክርስቲያን ስም ከልብ ይማጸናል።
3ኛ/ በዚህ አጋጣሚም የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥትም ለቤተ ክርስቲያን አንድነት የሚጠበቅበትን የበኩሉን አስተዋጽኦ በአግባቡ እንዲያደርግ በአክብሮት እንጠይቃለን።
4ኛ/ በመላው ዓለም ያሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች ሊቃነ ጳጳሳት፣ ማኅበረ ካህናትና ሕዝበ ክርስቲያን ሁሉ ቤተ ክርስቲያንን አንድ በማድረጉ ታሪካዊ ሒደት ላይ በጾም፣ በጸሎትና በሚያስፈልገው ማናቸውም ነገሮች ሁሉ ተገቢውን ድጋፍ በመስጠት ለቤተ ክርስቲያን አንድነት ይሠሩ ዘንድ በትሕትና እንማጸናለን።
 በመጨረሻም አምላከ አበው እግዚአብሔር የቅዱስነታቸውን ነፍስ ከማኅበረ አበው ኄራን እንዲደምርልንና ለመላው የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት፣ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን እንዲሁም ለቅዱስነታቸው ቤተ ሰቦች ሁሉ መጽናናትን እንዲሰጥልን ከልብ እንመኛለን።
የቅዱስነታቸው በረከት አይለየን።
የቤተ ክርስቲያንን ሰላምና አንድነት ያሳየን!
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ።


Tuesday, June 19, 2012

Hasband & Wife conversation




This is a conversation between Husband & Wife who are in Computer Field.

HUSBAND: Hi Dear, I am logged in.

WIFE: Would you like to have some snacks?

HUSBAND: Hard disk full.

WIFE: Have you brought the saree?

HUSBAND: Bad command or file name.

WIFE: But I told you about it in the morning!

HUSBAND: Syntax error, abort, retry, cancel.

WIFE: HAE BHAGAWAN! Forget it, where’s your salary?

HUSBAND: File in use, read only. try after some time.

WIFE: Atleast give me your credit card, I can do some shopping.

HUSBAND: Sharing violation, access denied.

WIFE: I made a mistake in marrying you!

HUSBAND: Data type mismatch.

WIFE: You are useless!

HUSBAND: By default.

WIFE: Who was there with you in the car this morning?

HUSBAND: System unstable. Press ctrl, alt, del to reboot.

WIFE: What is my value in your life?

HUSBAND: Unknown virus detected.

WIFE: Do you love me or your computer?!


HUSBAND: Too many parameters.

WIFE: I will go to my dad’s house!

HUSBAND: Program performed illegal operation, it will close.

WIFE: I will leave you forever!

HUSBAND: Close all programs and log out for another user.

WIFE: It’s worthless talking to you!

HUSBAND: Shut down the computer.

WIFE: I am going!!!

HUSBAND: It is now safe to turn off your compute

source -quatero

Sunday, June 10, 2012

ኢትዮጵያ ግብረሰዶምንና አራማጆቹ ምዕራባዊያንን አወገዘች

         ዓለም በሚያስገርም ሁኔታ እየተለዋወጠች ነው :: የአገራት መሪዎች ፣ታዋቂ የተባሉ ሰዎች እና አንዳንድ የኃይማኖት ተቋማት ኃጢአት ህጋዊ ይሆን ዘንድ ሲከራከሩ ይሰማል:: ይልቁንም ግብረ ሰዶም ሕጋዊ እንዲሆን ራሳቸው ፈቅደው ሌሎች እንዲፈቅዱ የተለያዩ ተጽዕኖ እየፈጠሩ ያሉ መሪዎች ተበራክተዋል:: ይህን አስመልክቶ በኢትዮጵያ የሚገኙ የተለያዩ ሃይማኖት ተቋማት የወሰዱት እርምጃ ይበል የሚያሰኝ ነው እንላለን::  
ኢትዮጵያ ግብረሰዶምንና አራማጆቹ ምዕራባዊያንን አወገዘች 

Wednesday, May 9, 2012

ለንግሥ ወደ ደቡብ ወሎ የተጓዙ 17 ሰዎች በመኪና አደጋ ህይወታቸው አለፈ::

ለንግሥ ወደ ደቡብ ወሎ የተጓዙ 17 ሰዎች በመኪና አደጋ ህይወታቸው ማለፉን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘገቧል::
እግዚአብሔር ነብሳቸውን ይማርልን::

በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን አማራ ሳይንት ወረዳ በምትገኘውና ዛሬ በምትነግሠው ርእሰ አድባራት ተድባበ ማርያም ገዳም ለንግሥ በመጓዝ ላይ የነበሩ 17 ሰዎች፣ በደረሰባቸው የመኪና መገልበጥ አደጋ ከትናንትና በስቲያ ሕይወታቸው ማለፉን በስፍራው የነበሩ የዓይን እማኞች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡ ከትናንት በስቲያ ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ሲሆን በደረሰው የመኪና መገልበጥ አደጋ 17 ሰዎች ወዲያውኑ ሕይወታቸው ማለፉን፣ ሁለት ሰዎች ወደ ደሴ ሆስፒታል መላካቸውን፣ ሁለት ደግሞ ሳይንት አጅባር ህዳር 11 ሆስፒታል መግባታቸውንና አንድ ተጐጂ ደግሞ ሳይንት አጅባር ጤና ጣቢያ ዕርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኙ እማኞቹ ተናግረዋል፡፡

ሕይወታቸው ካለፉት 17 ሰዎች መካከል አሥሩ እዚያው ተድባበ ማርያም ገዳም የቀብር ሥርዓታቸው በትናንትናው ዕለት ከምሽቱ 11 ሰዓት መፈጸሙን፣ የቀሪዎቹ አስከሬን ወደ አዲስ አበባና ወደየመጡበት አካባቢ እየተሸኘ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡

ከአዲስ አበባ በ600 ኪሎ ሜትርና ከሳይንት አጅባር በ40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው የተድባበ ማርያም ገዳም ለመድረስ ጥቂት ርቀት ሲቀር ባለው ገደላማ ቦታ ላይ ሲደርስ፣ አንድ መነኩሴና ሁለት ወጣቶች ወርደው በእግራቸው መጓዝ በመጀመራቸው ከአደጋው መትረፋቸውን እማኞቹ ገልጸዋል፡፡ በመኪና አደጋው ሕይወታቸው ላለፈውና የቀብር ሥርዓታቸው በዚያው በገዳሙ ለተፈጸመው ምዕመናን ብፁዕ አቡነ ገብርኤል በተገኙበት በፈረንሳይ አቦ ቤተ ክርስቲያን ትናንት ምሽት ላይ ፀሎተ ፍትሐት መደረጉን ምንጮች ገልጸዋል፡፡

Thursday, May 3, 2012

የታክሲ ውስጥ ጥቅሶች

ከብስራት እይታ ብሎግ የተወሰደ
 
‹ ክቡራን ተሳፋሪዎቻችን በአገልግሎት አሰጣጣችን ላይ አስተያየት፣ቅሬታ፣ትዝብት ወይም መሻሻል አለበት የምትሉት ነገር ካለ አንቀበልም!! መውረድ ይቻላል ››

ድሮ ልጅ በነበርን ጊዜ የትምህርት መፅሐፍትን ማንበብ ጎበዝ ስለሚያስብለን ማንበብ አሁንም ማንበብ ነበር ስራችን ፡፡ የህፃንነት አህምሮ እንደጉልምሳ ብዙም ስለማያስቸግር የተሰጠውንና የገባውን ነው የሚቀበለው፡፡ በወቅቱ ከትምህርት መፃህፍት ውጪ ማንበብ ጊዜን አልባሌ ቦታ እንደማዋል እና ከዓላማ መሳቻ ነው ተብሎ ስለሚታሰብ ከጥቂቶች በስተቀር በአብዛኛል ተማሪ አትኩሮቱ ደብተሩና ተያያዥነት ያላቸው መፅሐፍት ላይ ነበር፡፡ ምናልባትም ወላጆች ያሳደሩት ተፅዕኖ ሊሆን ይችላል፡፡ ታዲያ ይህን አልፎ ሁሉን አቀፍ ዕውቀት ያለው ተማሪ ማግኘት ብርቅ የነበረ ሲሆን ከተገኘም ጓደኛ ለማድረግ ተመራጭና ቅድሚያ ይሰጠው ነበር፤ እንደጎበዝ ይቆጠራል፡፡ ‹‹ እሱ ወይም እሷ ያላነበበው/ያላነበበችው መፃህፍት፤ ያላነበበው/ያላነበበችው ልቦለድ የለም ›› ይባላል፡፡
አንባቢ ነው የተባለውም ተማሪ መለያው ምልክቱ ደብተሩ በአባባሎችና ጥቅሶች ያሸበረቀና የደመቀ መሆኑ ነበር፡፡ የግሪኩ ፈላስፋ የተናገረው፣ የአረቦች አባባል፣የቻይናዎች አባባል፣ የኢትዮጵያውን ብሂል ወዘተ. . . ወዘተ . . . እየተባለ የተገኘው ይፃፋል፡፡ ምንጭ ይጠቀሳል፡፡ በሆነ አጋጣሚ ደብተሩን ያየ ወይም ያገኘ የተፃፈውን ፅሑፍ እና አባባል ኮርጆ ለራሱ ያደርገዋል፡፡ ታዲያ ማንም ተማሪ ጋር የሌለ ጥቅስና አባባል የሚፅፍ የሚናገር ‹‹ እሱ እኮ! ፤ እሷ እኮ !›› ይባልላቸዋል፡፡

ሌላው በትምህርት ቤት ህይወት ውስጥ የመለያያ ወቅት የሚባሉት ማለትም ተማሪዎች የሚለያዩበት 8ኛ፣10ኛ ወይም 12ኛ ክፍል ሊሆን ይችላል የሚዘጋጅ በተለምዶ ‹‹ ማስታወሻ ደብተር (Autograph) ›› ተብሎ የሚጠራ በዛ ያሉ ጥያቄዎችና መጠይቆች ያሉበት ለየት ያለ ማስታወሻ ይዘጋጅ ነበር፡፡ ማስታወሻ ደብተሩ ላይ ጽጌሬዳ አበባ መሳል፣ግጥሞች መፃፍ የተለያዩ አስገራሚና አስቂኝ የሚባሉ ፅሑፎችን ማውጣት ዋና ስራ ነበር፡፡ ሁሉም አለኝ የሚለውን ይፅፋል፤ ያነበበውን ያካፍላል፤እራሱን ከሌሎች ጋር ያወዳድራል እንዲሁም እራሱን ሊያሳይ ይጥራል፡፡

ትንሽ ቆይቶ በአካልም በአስተሳሰብም እያደግን ስንመጣ ያ ሁሉ ነገራችብ ላይ መቀዛቀዝ ይታያል፡፡ ማንበብ ባይተው እንኳን ለጥቅሶችና ለአባባሎች ያለን አትኩሮት ይቀንሳል፤ተፅዕኗቸውም ይወርዳል፡፡ የዛሬን አያድርገውና በአንድ ወቅት በየመኖሪያ ቤቱ ግድግዳ ላይ በጥሩ የእጅ ፅሑፍ የተፃፉ አባባሎችን፣ ግጥሞችን ማየት የተለመደ ነበር፡፡ ብዙዎቹ አስተማሪና መካሪ ለሠዎች ቀና እንድንሆን፣ ወንጌልን የሚሰብኩና እግዚአብሔርን የሚማፀኑ ጥቅሶች ነበሩ፡፡ አንዳንዴም አሽሙሮችም አይጠፉበትም፡፡ በወቅቱ እንዲህ ዓይነት ነገሮችን ማግኘት የሚቻለው በ‹‹ጠላ›› ወይም ‹‹አረቄ›› እንዲሁም ጠጅ ቤቶች አካባቢ ነበር፡፡ ምናልባት የሰከረን ለመምከር፣ ለማስተማር ወይም ብሶቱን ከፍ ለማድረግ ይሁን አይሁን አላውቅም፡፡ የዋህ እና ደስ የሚል ጊዜ ነበር፡፡ታዲያ አሁንስ?

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ደግሞ በታክሲዎች ውስጥና ውጪ የምመለከታቸው ነገሮች የድሮ እና ያለፉትን ጊዜያቶችን ያስታውሳሉ፡፡ በተለይ በአሁኑ ግዜ በያንዳንዱ ታክሲ ውስጥ ጥቅስና አባባሎች ማየት እየተለመደ ከመምጣቱም በላይ እንደአንድ የመግባቢያ መንገድ መቆጠርም ጀምሯል፡፡ እንደያኔው ባይበዛም አስተማሪና ምክር አዘል ነገር በጥቂቱም ቢሆን አላቸው፡፡ ነገር ግን ብዙዎቹ የማሳቅ ይዘት ያላቸውና በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ለአንድ ለሚመለከተው አካል መልዕክትን እንደ ማስተላለፊያ ዘዴ ይጠቀሙበታል፡፡ እነዚህ ጥቅሶች ፖለቲካዊ፣ ሀይማኖታዊ እንዲሁም አሽሙራዊ ንግግሮች ከፍ ሲልም ስድቦች ያካትታሉ፡፡


አንድ ግለሰብ የሚፈልገውን መልዕክት በቀላሉ ለብዙሀን ለማስተላለፍ ካሻው ከፅሑፍ የተሻለ ነገር አማራጭ የለም፡፡ ሀሳባችንን፣ ስሜታችንን፣ ደስታችንን፣ ሀዘናችንን የሆነውን፣ ያሰኘነንን በመግለፅ ያለምንም ድካም የተፈለገውን ግብ መምታት ይቻላል፡፡ በተለይ በታዳጊ ሀገራት የታሻውን በቀላሉ ማግኘት ስለማይቻል መልዕክትን በቀላሉ ለሚመለከተው ክፍል ማድረስ ይከብዳል፡፡ በታክሲዎቻችንም ላይ የሚታየው ይኸው ነው፡፡ ባለታክሲዎቹ ተሳፋሪዎቹ ጋር የያዙትን ግብግብ፡፡ ከተሳፋሪ ጋር ያላቸው ቀረቤታ እና ቅራኖ ያሰለቻቸው ነው የሚመስለው በሚመስል መልኩ የተለጠፉት ጥቅሶችና አባባሎች በሙሉ ሹፌሩን እና እረዳቱን የሚደግፉ፣ የሚያበረታቱ አትንኩን የሚሉ ናቸው፡፡ እርግጥ ነው በራስ ንብረት ላይ ሌላን ማሞገስ እና ማወደስ ሊከብድ ቢችልም የአብዛኛው ታክሲ ነጂዎች ስሜት ይመሳሰላል፡፡

ጥቂት ታክሲዎች ላይ ቢሆንም ተሳፋሪን የሚደግፉ ፅሑፎች ተመልክቻለሁ፡፡

ልክ እንደጊዜውና ወቅቱ የአባባሎቹ እና ጥቅሶቹ ይዘትና ዓላማ ይቀያየራል፡፡ ብዙዎቹ ግን የሚያተኩሩት መንግስትን የሚቃወሙ፣ የሚደግፉ፣ የሀገር ፍቅርን የሚገልፁ፣ ሀይማኖታዊ ይዘት ያላቸው፣ ስፖርት ተኮር ናቸው፡፡

እነዚህ የታክሲ ላይ ፅሑፎች ድሮ በየጠጅ ቤቱና ጠላ ቤቱ ከሚፃፉት የሚለዩባቸው አንዳንድ ነጥቦች አሉ፡፡ በዋናነት ግን የድሮዎቹ በቀጥታም ቢሆን መልካም ስሜትን ለመፍጠር ይሞክራሉ፡፡ ማለትም ጠንክሮ ስለመስራት፣ መበደል ቢኖር መቻልን፣ ክፉ አለመመኘትን፣ እና የመሳሰሉትን ትንሽም ቢሆን ፈሪሃ እግዚአብሔርን ይሰብካሉ፡፡ አንባቢውም ይሁን ጠጪው በዚሁ ቀለበት ውስጥ ያለ ነው፡፡ እንዳሁኑ ባይሆንም ቦታ ይሰጡታል አሁን የምናያቸው ግን ከላይ ያልኳቸውን ነገሮች ያካተተ ቢሆንም ብዙዎቹ ግን ‹‹እኔነት›› ስሜት አለባቸው፡፡ አትንኩኝ፣ ሂዱልኝ የሚሉ ብሶታዊ አንድምታ አላቸው ፡፡ መማረርና ጨለምተኝነት ይሰብካሉ፡፡በእርግጥ መልካም ሀሳብንም የያዙ አሉ፡፡

አንዳንዶችም የመፅሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ይጠቀማሉ፡፡ እነዚህም ቢሆኑ ከአቅም በላይ የሆነ ነገር እንዳለ ጠቋሚዎች ናቸው፡፡ ‹‹ለሚያልፍ ቀን ክፉ አትናገር›› . . . . ‹‹ የጌታ ፍቃድ ይሁን ብለን ዝም አልን››. . . . ‹‹እግዚአብሔር ይፈርዳል›› . . .ወዘተ. . . መፅናናትን ተስፋ አለመቁረጥን አይዞን፣እንጠንክር ይላሉ፡፡ ፍርሃትን ፈጣሪዎች ናቸው፡፡በጊዜው ሁኔታ የፈጠረው እንደሆነ ባላውቅም ግን የሆነ የጎደለ ነገር እንዳለ ያሳያል፡፡

ስነፅሑፍ በጊዜያትና በትውልዶች መካከል በራሱ መንገድ የሚሄድና የሚለወጥ ጥበብ እንደመሆኑ የድሮን የአፃፃፍ ጥብበና ይዘት በዚህ ዘመን መጠበቅ የዋህነት ሊሆን ይችላል፡፡ ያም ቢሆን የምንፅፋቸው ነገሮች የራሳቸውን የሆነ መልዕክትና ተፅዕኖ ሊፈጥሩ እንደሚችሉ ከግምት ውስጥ መግባት ይኖርበታል፡፡እኛም ሁሌም ልንማር፣ ልናውቅ ፣ ልንጠይቅ እራሳችንን የተሻለ ለማድረግ መጣር ይኖርብናል፡፡

ከማጠቃለሌ በፊተ ስለታክሲ ጥቅሶች ማውራታችን ካልቀረ እስቲ የታዘብካቸውንና ያነበብኳቸውንና ትንሽ ፈገግ ያደርጋሉ ያልኳቸውን ላካፍላችሁ፡፡



· የታክሲ ከሌለህ ወርደህ በባስ ሂድ· ሠውን ማመን ተፈራርሞ ነው· ፍቅር ካለ ባጃጅ ባስ ይሆናል
·
በቴሌቶን ሂሳብ መክፈል ክልክል ነው
·
ሒሳብ ሳይከፍሉ ሀሳብ አይጀምሩ
·
ለፀባይኛ ተሳፋሪ የፀባይ ዋንጫ እንሸላማለን

· ለስራ ነው የወጣነው

· በመጀመሪያ የጋለ ደምህን ተቆጣጠርና ሀሳብህን ግለፅ
·
ባለጌና ዋንጫ ከወደአፉ ይሠፋል
·
ኤች.አይ.ቪንና የጫማ ሽታን በጋራ እንከላከል
·
ማንችስተር ያሸንፋል አርሠናል ለዘለዓለም ይኑር

· ሠው አካውንት ይከፍታል አንዳንዱ አፉን ይከፍታል

· ሞባይል ለጣለ ሲም እንመልሳለን

· ሹፌሩን መጥበስ ክልክል ነው በነገር

· ሠው ብቻ ነው የምንጭነው በስህተት የገባ ይውረድ

· ታክሲ ለሚጠቀሙ ብቻ

· ክቡራን ተሳፋሪዎቻችን በአገልግሎት አሰጣጣችን ላይ አስተያየት፣ቅሬታ፣ትዝብት ወይም መሻሻል አለበት የምትሉት ነገር ካለ አንቀበልም!! መውረድ ይቻላል::

· ለሠው ቅን ሁን እንጂ ቅንቅን አትሁን

· ማስቲካ የሚታደል መስሎአችሁ አፋችሁን እንዳትከፍቱ

· መስኮቱን በመክፈት ለትራፊክ ፖሊስ አያጋፍጡን!

· ጤነኛ ካልሆኑ መውረጃዎ ደርሷል

· በጭነት መኪና መታችሁ እዚህ ትቀናጣላችሁ

· የክፍለ ከተማ ሠዎች ካላችሁ ሒሳብ በቅድሚያ

· ኑሮአችሁ ሳይሞላ "ታክሲው አልሞላም?! " ትላላችሁ!· ጥብቅ ማሳሰቢያ ለክቡራን ሌቦች ሒሳብ ሰብስበን ሳንጨርስ ስራችሁን

መጀመር አትችሉም! የማይስማማ ሌባ ካለ መውረድ ይችላል፡፡

· ለዓለም ሙቀት መጨመር መንስዔው ጭቅጭቅ ነው

· ይህ ታፔላ የሚሉት ከመጣ ፤ ምሳችን በቆሎ ራታችን ቂጣ

· ታክሲው ሳይቆም መውረድ ይቻላል፡፡

· እንዴት ጭት አትቃሙ ይባላል፣ ሰርቶ የማይዝናና አህያ ብቻ ነው



· የበታችነት ከተሰማህ ዛፍ ላይ ውጣ

· ስልጣን ህዝብን ማገልገያ እንጂ ማስፈራሪያ አይደለም

· የቤትህን አመል እዛው!!!

· የሠው ትርፍ የለውም . . . ተጠጋጉ!

· በታክሲ. . . . . ህግ አላውቅም

· ታክሲና መንግስተ ሰማያት ሞልቶ አያውቅም

· ለታላቅ መልስ አይሰጥም

· ነገን ለመኖር መጀመሪያ ዛሬን ኑር..በመቃም

· ‹‹ደሀ›› ከፍ ብሎ የሚታየው ባስ ላይ እና እራሱን ሲሰቅል ብቻ ነው፡፡

· እባክዎን የአባይ ቃል ስላለብን ጠጋ ጠጋ ይበሉልን

· ለካፌና ለላዳ ብዙ ይከፍላሉ፤ እኛ ጋ ሲሳፈሩ ለምን ይጨቃጨቃሉ


በመጨረሻ
ተሳፋሪ፡- የሰጠከኝ ልክ አይደለም፤ሒሳብ አትችልም
" ? አልተማርክም? ደደብ . . . .
ወያላ፡- ጋሼ ድንጋይ ለመጫን እስከ ሁለተኛ ክፍል መማር በቂ ነው

አበቃሁ፡፡